ባለፉት 44 ዓመታት  ስለ ኢትዮጵያ ዙፋን በማርክሲስቶች  የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ቅጥፈት ታቅዶበት  በጣም አሳፋሪና መርዛማ የሆነ የተንጋደደ  መርጃ በዘር ፖለቲከኞች ሲስፋፋ ቆይቷል። ለውጭ  በሚሰሩና በውጭ ሀገራት ሰላዮች አማካይነት የስመ  ጥሩውን የሰሎሞናዊውን ዙፋን ለመመረዝ፤ በደርግ ጊዜና  ከደርግ በኋላ ለተወለዱት ልጆች ይህንን ሲመግቧቸው ኖረዋል። ይህንን  የሀሰት ወሬ በወቅቱ አልተቃወምንም። ስለዚህም ይህ የውሸት ወሬ ከዚህ  በታች በሚዘረዘሩት ሰባት ነጥቦች እውነቱን እንደሚያሳያችሁ እምነቴ ነው። እኔም ይህንን  የምጽፈው ለጭቅጭቅ ወይም ለመነታረክ ብዬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ውለታና ክብር ስል ነው።

1ኛ ሐሰት፦  የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ሥርዓት  ፊውዳል ነው፤ የሕዝብን ተሳትፎ አይፈቅድም  ነበር የሚል ውሸት ነው።

ይህ ውሸት የኢትዮጵያ ዘውዳዊ ሥርዓት  ሙሉ ለሙሉ እንደ አውሮፓውያን ሳይሆን የሕዝቡንም ተሳትፎ ይፈቅድ ነበር። የእያንዳንዱ ጠቅላይ ግዛት፣ አውራጃና፣ ወረዳ  የራሱ የዘውድ ተወካይ የነበረው ሲሆን እነዚህም ተወካዮች የሕዝብ ምክርቤት ውስጥ መቀመጫ ነበራችው።

2ኛ፦  ዲሞክራሲ  ከሕገመንግስታዊ  ዙፋን ይሻላል።

በአሁን ጊዜ ውስጥ ያለው የጎሳ  አሰራር ሕዝቡን ቤትና መሬት አልባ  አድርጎታል። በገዛ ሐገሩ ላይ ሕዝቡ  ምንም አይነት ተሰሚነት የሌለውና ውሳኔዎች  ሁሉ በውጭ አገር ሰዎች የፈለጋቸውን የሚያደርጉበት  ሆኗል። በአንጻሩ ደግሞ የዘውድ አሰራር የሕዝብን ጥቅም  የጠበቀና፤ የእያንዳንዱን ዜጋ ሰላምና ጸጥታ ያስከበረ፤ ወደፊትም   የሚያስከብር ነው። ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ ታላቋ ብሪታንያ ፣ኖርዌይ፣ ስዊድንን  መመልከት ይበቃል። የዘውድ አሰራር ረዘም ላለ ጊዜ ለሀገር ማሰብ ይችላል።

3ኛው ውሸት፦ የኢትዮጵያ  ነገሥታቶች ስለድሀው ግድ  የላቸውም የሚል ነው።  

ባለፉት 45 ዓመታት  ውስጥ ከተነገሩት ውሸቶች መካከል  ከፍተኛ ጉዳት ያመጣውና የወጣቱን አእምሮ  የበከለው ይህ ውሸት ነው። ደርግ ይህንን ውሸት  ያስፋፈበት ምክንያት ብቻውን ሀገሪቱን ለመዝረፍ ስለወሰነ  ነው። ይህን ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ለ3000 ዓመታት በንጉሦች  በተዳደረችበት ዘመን አንዳንድ ክፉዎች አልነበሩም ማለትም አይደለም። ለምሳሌ በዘመነ መሳፍንት ጊዜ  ብዙ መሳፍንቶች ብዙ ሕዝብን ያጉላሉ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል። ይህም ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያ ከአንገቷን  ቀና ብላና ጎልታ እንድትታይ፤ እንደዚሁም ከባርነትና ከቅኝ ግዛት ያዳኗት ንጉሶቹ ብቻ ናቸው። መንግስቱ ኃይለማርያም  500 ሺ የራሱን ዜጋ ሲገድል፣ መለስ ዜናዊ በበኩሉ አፓርታይድን ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያስተዋውቅ አገራችንን ይህ ነው  የማይባል እልቂት ውስጥ ጨምረዋታል። ነገሥታቱ ግን አገራችንን እንደዚህ ዓይነት ቅሌት ውስጥ እንዳትገባ ጠብቀውና ተንከባክበው  በክብር አኑረውናል። እነሱም አልፈዋል።የኢትዮጲያ ዘውድ ታሪክ የተጀመረው ኮሚኒሲቶቹ እንደሚዋሹት በ19ነኛውና በ20ኛው ክፍለ ዘመን  አይደለም። ኢትዮጵያ ዘውዳዊ ሥርዓት በጣም ቆዩ ከሚባሉ ዘውዶች አንደኛው ነው።

4ኛ ውሸት፦  የኢትዮጵያ ዘውድ  የሚወክለው ኦርቶዶክስ  ሃይማኖትን ብቻ ነው። 

የኢትዮጵያ  ዘውድ ብዙው አውታር  የሆኑት መሰረቶቹ ከብሉይ  ኪዳን የወጡ ናቸው። ኢትዮጵያ  የይሁዳ አንበሳ የምትባለውም በዚህ ምክንያት ነው።  የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንጉሥ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከእናቱ  ንግሥተ ሳባና ከአባቱ ንጉሥ ሰሎሞን ይወለዳል። ልጅ ቴዎድሮስ  ፍቅረማሪያም ሊያስረዳ እንደሞከረው እነዚህ ታሪኮች በክርስትና ብቻ ሳይሆን በአይሁድና  በእስልምና ዘንድም ይታወቃሉ ። እነዚህ ሶስት ሐይማኖቶችም በኢትዮጵያ ተከብረው ይኖራሉ። ኢትዮጵያ በመጽሀፍ  ቅዱስ ውስጥ ከማንኛውም ሀገር በላይ ስሟ የሚነሳ ነች። በእስልምናም እንደሚታወቀው ነቢዩ መሐመድ ችግር ውስጥ  በገባበት ጊዜ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደጠበቀውና፣ እንደረዳው ታሪክ ይመሰክራል። ኢትዮጵያ የአማኞች ሀገር ናት፤ የኢትዮጵያ  ነገሥታትም እንደ አስፈላጊነቱና ግዜው በጠየቀው መሰረት በእኩልነት ሲያስተዳድሩዋቸው ኖረዋል። የኢትዮጵያ ነገሥታቶች አንዱን ሃይማኖት  ከሌላው አስበልጠው አያውቁም።

5ኛው ውሸት፦  ስላለፈው ከማሰብ  ይልቅ በኢኮኖሚ ብንበለጸግ  ይሻላል።

ማንኛውም  ሀገር የራሱን  ታሪክ ማስተዋስ ካልቻለ ይጠፋል።  የውጪውን በኃይል እየተቀብልንና እያከበርን  በራሳችን ላይ ስናሾፍና ስናላግጥ ቆይተናል።  ሰንደቅ ዓላማችንን እንኳን ንቀን በጣሊያንኛው ባንዲራ  ስንለው ቆይተናል። ይህንን ስንል ለሰንደቅ አላማችን በአድዋና  በማይጨው የሞቱት አያቶቻችን መቃብር ላይ እንደደነስን ይቆጠራል።  በአንድ በኩል ቅኝ ተገዝተን አናውቅም እያልን በሌላ በኩል በገዛ ባህላችን  በታሪካችንና በተሰዉልን ንጉሦች እናላግጣለን። ለወደፊቱ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር እራሳችንን ማክበርና የራሳችን የሆነውን በቅጡ መጠበቅ ነው። ከዚህም በላይ የኢኮኖሚ ብልጽግና ተብሎ ጥቂቶችን አበልጽጎ ብዙውን የሚያደሀይና እዳና ብድር ውስጥ ከዛም ልመና ውስጥ ከዘፈቀው የኢኮኖሚ ብልጽግና ሳይሆን የኢኮኖሚ ቀብር ነው። ከዚህ የኢኮኖሚ ውድቀትም ሆነ ባህላዊ ሰለባ የሚያወጣት መሪ አስፈላጊ ነው። ይህ መሪ ኢትዮጵያን የሚወድና ህዝቡዋን ያከበረ አስመሳይና ዘረኛ ያልሆነና ባለን አቅም ፖሊሲ ቀርፆ ማድረግ የሚቻለውን ብቻ የሚያደርግ መሆን አለበት። ኢትዮጵያን ወደ ሀብት ሊያመጣት የሚችለው የግል መሬት ሲኖርና የህባትሞችንና የድሆችን ሃብት የማይነጥቅና የግል ሐብትን የሚያከብር መንግስት ሲመጣ ብቻ ንው።

6ኛው ውሸት፣ የኢትዮጵያ ዘውድ የሚወክለው አማራውን ብቻ ነው፣ 

በአሁኑ  ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ  ጎልቶ እየታየ ያለው አስቀያሚ  የሆነው የዘረኝነት አመልካከት ከዓመታት  በፊት በጭራሽ አልነበረም። ባለፉት 44 ዓመታት  የታየው አስጠሊ ጎሰኝነት በቀድሞ ንጉሣዊ ሥርዓት ውስጥ  ያልነበረ አስቀያሚ ክስተት ነው። በአባቶቻችን ዘመን ከሀገር  በፊት ዘርን ማስቀደም በጣም አሳፋሪና ነውርም ነበር። አገራችን  ኢትዮጵያ ውስጥ ንጹህ የዚህ ጎሳ ወይም ዘር የሚባል ሰው የለም። ያለፉት ነገሥታትም  ቢሆኑ ከሁሉም ዘር ደም ያላቸው ነበሩ። ይህንን ስንል ደግሞ ባለፉት ዘመናት የተበድሉ  ወይንም በባርነት የተሸጡ ሰዎች የሉም ለማለት አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማንኛውም ሀገር           አለ አግባብ የተጎዱና የተጎሳቀሉ ሰዎች ነበሩ። ለወደፊቱ ግን የሚበጀን ይህ ጎሳ ያኛውን ጎሳ በድሏል ብለን  በመወነጃጀል ሀገራችንን እንደ ዩጎዝላቪያና፣ ሩውንዳ በእርስ በርስ ጦርነት ከማጥፋታችን በፊት ቆም ብለን እንድናስብበት  ይገባል።

7ኛ ውሸት፦ ኢትዮጵያ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ዘመናዊነት ይስፈልጋታል፣

ለ3000  ዓመታት የሰራልንን  ሥርዓት አጣጥለን ዘመናዊነትን  ባልሆን አቅጣጫ ልናመጣው ስለሞከርንን  ባሁን ጊዜ የውዳቂ ልብስና የተለመነ ስንዴ  አስመጪዎች ሆነናል። ባለፈው ሰሞን አንድ ጋዜጣ  ላይ ሳነብ ኢትዮጵያና ሴነጋል ብዙ ቆሻሻ ሰብሳቢ  መሆናቸውን ይናገራል። ይሄን ሳነብ በኩሩ ኢትዮጵያዊነቴ በጣም  እፍረት ተሰምቶኛል። በዚህ ዓለም ላይ በብዙ ሰዎች ስንደነቅ የነበርን  ህዝቦች ወርደን ወደ ልመና ገብተንና በእርዳታ ሰጪዎች እጅ ሥር መኖራችን  ያሳዝነኛል። ዘመናዊነት ይህ ከሆነ በአፍንጫችን ይውጣ። እኔ በበኩሌ በዘመናዊነትና  በመለወጥ አምናለሁ። ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ኑሮን ማቅለል ሁሉን ሰው ሀብታም ማድረግ አንደዚሁም  ከሁሉ በፊት በሁሉ ነገር ቀድሞ መገኘት አለብን። እነዚህን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች  ካደረግን ኢትዮጵያን ሀብታም ማድረግ እንችላለን። 

  1. ጠንክሮ መስራት፣
  2. የጀመርነውን መጨርስ፣ 
  3. ለቤተስባችንና ለራስችን ብቻ መስገብገብ ማቆም፣
  4. የሰውን ንብረት በግፍ መንጠቅ ማቆም፣
  5. ውሸት መናገርን መተው፣ 
  6. ሚስጥረኛ አለመሆን፣
  7. ከሰው በልጦ መታየት መሞከርን ማቆም፣
  8. ሌላ ሰው የሰራውን ስራ ማጣጣል ማቆም፣
  9. ሳንሰራና ሳንደክም ጨዋታና ምግብ መውደድን መተው፣ 

በመደምደሚያም  ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት  የሐሰት ዘመናዊነት የማትፈልግ፣ የራሷ የሆነ በቂ  እምነት፣ ታሪክ፣ ሥነ ሥርዓት፣ ስነፅሑፍ፣ ባህል፣ አመለካከት፣ ያላትና አራሷን ለ 3000 ዓመታት  ስትመግብ የኖረች ነበረች። ወደፊትም እነዚህን ነገሮች አሻሽለንና በሀገራችን አሳሳቢ የሆነውን  የሕዝብ ቁጥር ብዛት በአስቸካይ መቆጣጠር ከቻልን ኢትዮጵያ ሀብታም የማትሆንበት ሁኔታ አይኖርም። ሕገ  መንግሥታዊ የዘውድ አስተዳደር ኢትዮጵያን ለሚያስተዳድሩ ሰዎች ክብርና ድጋፍ ያመጣል እንጂ ጉዳት አይኖረውም።

Below is a video that Ethiopians for Constitutional Monarchy produced that at once gives respect to the rich history of the Ethiopian Monarchy while paying homage to the Ethiopian people who are the crown jewels of our nation. Like our page on Facebook by clicking HERE.